Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵየ የዓለም አቀፍ  የወጣት ስራ ፈጣሪዎች ጥምረት አባል ሆነች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵየ የዓለም አቀፍ የወጣት ስራ ፈጣሪዎች ጥምረት አባል ሆናለች፡፡

በቻይና ተነሳሺነት የተመሰረተው የዓለም አቀፍ የወጣት ስራ ፈጣሪዎች ጥምረት ጉባኤ በቻይና ቤጂንግ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩም ኢትዮጵያን በመወከል የኢትዮጵያ ወጣቶች የስራ ፈጠራ ማህበር ፕሬዚዳንት ሳሚያ አቡዱልቃድር ተሳትፈዋል፡፡

በጉባኤው ኢትዮጵያ የጥምረቱ አባል ሆና የተመረጠች ሲሆን÷ ለቀጣይ ስራዎች ስምምነት መፈረሙን ሳሚያ አቡዱልቃድር ተናግረዋል፡፡

ሳሚያ አቡዱልቃድር በጥምረቱ የአፍሪካን ሀገራት ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸውንም የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ  ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ሳሚያ አቡዱልቃድር በቤጂንግ ቆይታቸው የቻይና ባለሃብቶች የኢትዮጵያ ወጣት ስራ ፈጣሪዎችን መደገፍ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መምከራቸው ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ በሀገራችን ስላለው የኢንቨስተመንት አማራጭ ገለጻ ማድረጋቸውን አንስተዋል፡፡

የዓለም አቀፉ የወጣት ስራ ፈጣሪዎች ጥምረት 200 በላይ አባል ሀገራት ያሉት መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.