Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በሩሲያ ላይ የምታደርገውን ጫና ሃያላን ሀገራት እየተቃወሙት ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በሩሲያ ላይ የምታደርገውን ጫና ሃያላን ሀገራት እየተቃወሙት እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ህንድ፣ ብራዚል፣ደቡብ አፍሪካ፣ ፓኪስታን እና ሌሎች በኢኮኖሚ ያደጉ ሀገራት የባይደን አስተዳደር በሩሲያ ላይ የሚያደርገውን ጫና የተቃወሙ ሀገራት መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ራሽያን ታይምስ ከአሜሪካ የስለላ ሰነዶችን አገኘሁት ያለውን መረጃ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ÷ህንድ እየተካሄደ ባለው የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ከሁለቱም ጎን የመሰለፍ ሃሳብ እንደሌላት አብራርቷል፡፡

የህንድ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አጂት ኩማር ዶቫል ለሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፀሃፊ ኒኮላይ ፓትሩሼቭ ተናገሩት እንደተባለው÷ህንድ  ዩክሬንን እንድትደግፍ በምዕራቡ ዓለም የሚመጣባትን ግፊት እየተቃወመች ነው፡፡

ብራዚልም ዋሺንግተንን እና አጋሮቿን ከመደገፍ ይልቅ በዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ውስጥ የሽምግልና ሚና የመጫወት ፍላጎት እንዳላት ነው የተገለፀው፡፡

የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ በቻይና ባደረጉት ጉብኝት ወቅት የዩክሬን እና ሩሲያን ግጭት የምዕራባውያንን አጥቂ እና ተጠቂ ትርክት እንደማይቀበሉ መግለጻቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.