Fana: At a Speed of Life!

በቀን 288 ሺህ እንጀራ የሚጋገርበት ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በቀን 288 ሺህ እንጀራ የሚጋገርበትና እንጀራን ኢንዱስትራላይዝ በማድረግ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነው ለሚ እንጀራ ማዕከል ተመረቀ፡፡

ማዕከሉ ከ2 ሺህ እናቶች በተጨማሪ በተለያዩ የስራ መስኮች ለ1ሺህ ነዋሪዎች በአጠቃላይ ለ3 ሺህ ወገኖች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተለያዩ ከተሞች ከንቲባዎች ጋር በመሆን ማዕከሉን መርቀዋል፡፡

ለሚ እንጀራ ማዕከል የእናቶችን ድካም የሚያቀልና እንጀራን ከፍ ባለ ደረጃ ማምረት የሚያስችል መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ማዕከሉ ከፈተናዎቻችን በላይ ሆነን የማይቻል የሚመስለውን የመቻላችን ማሳያ ነው ብለዋ ከንቲባዋ፡፡

በየቦታው ያለንን አቅም፣ ገንዘብ እና እውቀት በማስተባበር የነዋሪዎችን ሸክም የሚያቀሉ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ እየተገበርን ሲሉ አመላክተዋል፡፡

ኦቪድ ግሩፕ 170 ሚሊየን፣ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 75 ሚሊየን፣ መድህን ድርጅት 20 ሚሊየን ብር፣ መታሰቢያ ታደሰ ኮንስትራክሽን 500 ዘመናዊ ምጣዶችን በማቅረብ እንዲሁም የታፑ ምግቦች ደግሞ በማማከር ለማዕከሉ ዕውን መሆን ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከንቲባ አዳነች በእናቶች ስም አመስግነዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.