Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየርሊጉ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

በሊጉ ተጣባቂ የነበረው የፋሲል ከነማ እና ሀድያ ሆሳዕና ጨዋታ በፋሲል ከነማ 2 ለ 1 አሸነፊነት ተጠናቋል፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

በሊጉ ተጠባቂ የነበረው የፋሲል ከነማ እና ሀድያ ሆሳዕና ጨዋታ በፋሲል ከነማ 2 ለ 1 አሸነፊነት ተጠናቋል፡፡

በጨዋታው ሀድያ ሆሳዕና በባየ ገዛኸኝ ጎል ሲመራ ቢቆይም ከረፍት መልስ ኦሴ ማውሊ እና ናትናኤል ገብረ ጊዮርጊስ ያስቆጠሯቸው ጎሎች ፋሲልን አሸናፊ አድርገዋል፡፡

አፄዎቹ ማሸነፋቸውን ተከትሎ በ33 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ሲችሉ ነብሮቹ ሀድያ ሆሳዕና ባንፃሩ ከነበሩበት  አንድ ደረጃ ዝቅ በማለት 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

በሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ 5 ቢጫ ካርዶች የተመዘዙ ሲሆን÷ የሀድያ ሆሳዕናው አጥቂ ባየ ገዛኸኝ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል፡፡

ቀደም ሲል ለገጣፎ ለገዳዲን የገጠመው ወላይታ ድቻ 2 ለ 0 ሲያሸነፍ ስንታየሁ መንግስቱ አበባየሁ አቺሶ ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡

የሊጉ 22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ ቀጥለው ሲካሄዱ  ባህርዳር ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ ፤ ኢትዮጵያ ቡና ከአዳማ ከተማ መርሃ ግብራቸውን ያከናውናሉ፡፡

 

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.