Fana: At a Speed of Life!

ኮቪድ 19 በኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰውን የከፋ ጫና ለመከላከል አስፈላጊ እርምጃዎች መውሰድ ይገባል- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ19) በኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰውን የከፋ ጫና ለመከላከል አስፈላጊ እርምጃዎች መውሰድ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ የሠራተኞችን የሥራ ዋስትናን ማስጠበቅ፣ ዘላቂ በሆነ መልኩ ገቢ እንዳይቋረጥ ማድረግ፣ እጅግ ተጋላጭ የሆኑትን የማኅበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ የሚያደርጉ አሠራሮችን ማስፋፋት፣ የመሠረታዊ አቅርቦቶችን የግብይት ሥርዓት ማርጋት፤ እንዲሁም ለአምራች ዘርፎች ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል።

በተጨማሪም “ለምግብ ዋስትናችን የግብርናውን ዘርፍ አምራችነት ማረጋገጥ ወሳኝነት አለው” ሲሉም አስታውቅዋል።

ምንም ዓይነት የአቅርቦት እጥረት እንዳይከሠት የማዳበሪያ፣ የምርጥ ዘር እንዲሁም የፀረ ተባይ መድኃኒቶች አቅርቦት ሳይቆራረጥ የሚቀጥል መሆኑንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ያስታወቁት።

የኢኮኖሚውን ዘርፍ መዳከም ሊያራዝሙ ከሚችሉ ሁኔታዎች አንዱ ተመጣጣኝ የሆነ የኅብረተሰብ ጤና ርምጃ አለመውሰድ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

“ለኢኮኖሚው መረጋጋት ሲባል በሕክምናው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ሙዓለ ንዋይ በማፍሰስ ተመጣጣኝ የመከላከል ርምጃ መውሰዳችንን እንቀጥላለን” ሲሉም ገልፀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.