Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ሚኒስትሯ በ24 ሰአታት ውስጥ ለ745 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ ሶስት ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ብለዋል።
ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ ሁለቱ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ አንዱ ደግሞ ቻይናዊ መሆኑም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት አንደኛው ኢትዮጵያዊ የ22 ዓመት ወጣት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆን፥ ጉዞ ታሪክ የሌለውና የስራው ባህሪ ተጋላጭነት ያለው መሆኑ ተገልጿል።

ሁለተኛው ኢትዮጵያዊም የ22 ዓመት ወጣት ሲሆን፥ ከሳዑዲ አረቢያ የመጠና በለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኝ መሆኑም ነው የተገለፀው።

በተጨማሪም ሶስተኛው ግለሰብ ቻይናዊ ሲሆን፥ በሰበታ ነዋሪ መሆኑ፣ የጉዞ ታሪክ እንደሌለው እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለውና እንደሌለው በመጣራት ላይ መሆኑንም አስታውቅዋል።

ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 114 ደርሷል።

ከእነዚህ ውስጥ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ 16 ሰዎች አገግመው፤ 93 ሰዎች ደግሞ በለይቶ ማቆያ ህክምና ላይ ይገኛሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.