Fana: At a Speed of Life!

የግል ትምህርት ቤቶች ለሰራተኞቻቸው ሙሉ ደመወዛቸውን እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ውሳኔ ተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የግል ትምህርት ቤቶች ለሚያስተዳድሯቸው ሰራተኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሙሉ ደመወዛቸውን እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ውሳኔ መተላለፉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ፥ በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ አሰራር ለመዘርጋት ውሳኔው መተላለፍን ገልጿል።

ውሳኔው ከመተላለፉ በፊት በቅድሚያ በ36 የግል ትምህርት ቤቶች የመስክ ዳሰሳ መደረጉን የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ገረመው ገልጸዋል።

ከዚም ባለፈ ከግል ትምህርት ቤቶች ማህበር ከወላጆችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ጭምር ውይይት ተደርጓልም ነው ያሉት።

በዚህም የግል ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ማስከፍል የሚችሉት ቀደም ባሉት ወራት ሲያስከፍሉት ከነበረው ከ50 እስከ 75 በመቶውን ብቻ ይሆናል ተብሏል።

ከዚያም ባለፈ ትምህርት ቤቶቹ ክፍያውን ሲጠይቁ ለሚያስተምሯቸው ተማሪዎች በተለያዩ መንገዶች ትምህርቱን ተደራሽ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም ተነግሯል።

ውሳኔው ትምህርት ቤቶች ትርፍን ታሳቢ ሳያደርጉ በስራቸው ያሉ ሰራተኞችን ታሳቢ አድርገው በመንቀሳቀስ  ለሰራተኞች ሙሉ ደመወዛቸውን መክፈል እንዳለባቸውም ነው የተገለጸው።

ተያይዞም ወረርሽኙ  ኢኮኖሚያቸውንም የጎዳው ወላጆች በረዥም ጊዜ ክፍያ እንዲከፍሉና ምንም መክፈል የማይችሉ ደግሞ መረጃ በማቅረብ ከክፍያ ነጻ እንዲሆኑ ተወስኗል።

ከዚያም ባለፈ የወላጅ ኮሚቴዎች ከትምህርት ቤቶች ጋር ጥብቅ ቁርኝት በመፍጠር መስራት አለባቸው ተብሏል።

ውሳኔዎቹ ለክልሎችም የተላኩ ሲሆን፥ ከሚያዝያ 12 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናልም ነው የተባለው።

በዙፋን ካሳሁን

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.