Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ሃገራት መሪዎች ጉብኝት በኢትዮጵያ እና በሀገራቱ መካከል ያለው ግንኙነት ወደ መተባበር መምጣቱን ያመላክታል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሃገራት መሪዎች በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝት በኢትዮጵያ እና አውሮፓ መካከል ያለውን ግንኙነት ከመጠራጠር ወደ መተባበር መምጣቱን ያመላክታል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ ከጀርመን ባለሀብቶች እና የንግድ ተቋማት ባለቤቶችና ጋዜጠኞች ጋር በኢትዮጰያ ጉብኝት ያደርጋሉ ብለዋል።

በቆይታቸውም ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ባለሃብቶች እና የንግድ ተቋማት ሃላፊዎች በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት እድል ተመልክተው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ስራዎች ይሰራሉም ነው ያሉት።

የአውሮፖ ሃገራት መሪዎች በኢትዮጵያ እያደረጉት በለው ጉብኝትና የተደረሱ ስምምነቶች ትልቅ ትርጉም ያላቸውና የጋራ ተጠቃሚነትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑንም ነው የገለጹት።

የሱዳን ወቅታዊ ጉዳይን በተመለከተው በሰጡት መግለጫም በሱዳን የሚገኙ ዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ እና ወደ ሃገር ቤት የመመለሱ ስራ በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

እስካሁን ከ3 ሺህ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገር ቤት ተመልሰዋል።

61 ሃገራት 7 ሺህ 726 የሚሆኑ ዜጎች በኢትዮጵያ አልፈው ዜጎቻቸውን ከሱዳን ማስወጣታቸውን በመጥቀስም፥ 75 የበረራ ፍቃድ እንደተሰጠም አንስተዋል።

በፍሬህይወት ሰፊው

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.