Fana: At a Speed of Life!

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከ135 – 250 ሚሊየን ሰዎች የረሃብ ስጋት ተደቅኖባቸዋል- ተመድ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዓለም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የረሃብ ስጋት ተደቅኖባታል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሃላፊ ዴቪድ ቤስሌይ በረሃብ ምክንያት የሚከሰተውን ከፍተኛ ቀውስ ለማስወገድ ፈጣን እርምጃ ያስፈልጋል ብለዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የወጣ ሪፖርት በረሃብ ምክንያት ከ135 ሚሊየን እስከ 250 ሚሊየን ሰዎች ጉዳት ሊደርስባቸው እንደሚችል አመላክቷል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም የረሃብ ስጋት የተደቀነባቸው ሀገራት በኢኮኖሚ ቀውስ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በግጭት ተፅዕኖ የደረሰባቸው 10 ሀገራት ናቸው ብሏል።

ሀገራቱም ኢትዮጵያን ጨምሮ የመን፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ አፍጋኒስታን፣ ቬንዜዌላ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ሶሪያ፣ ናይጀሪያ እና ሀይቲ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ሪፖርቱ እንዳመላከተው የደቡብ ሱዳን 61 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ባለፈው ዓመት የምግብ ቀውስ አጋጥሞት ነበር ።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.