Fana: At a Speed of Life!

በመቅደላ ወረዳ በግለሰቦች መካከል በተነሳ ግጭት የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ሞላ ለኢዜአ እንደገለፁት ችግሩ የተከሰተው ትናንት ከ8 ሰዓት ጀምሮ በወረዳው ቀበሌ 022 ኮሬብ ተብሎ በሚጠራው የገጠር ቀበሌ ነው።

በሁለት ግለሰቦች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት በተነሳው ግጭት የአንዱ ቤተሰብ አባላት ወንድማቸው በተቃራኒው ባለ አካል በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ ማለፉን ተናግረዋል።

በጉዳዩ የተበሳጩት የሟች ወንድሞች አለመግባባቱን ለማብረድ ወደ ቦታው ከሄዱ የፀጥታ አባላት ጋር በከፈቱት ተኩስ አራት ፖሊሶችን ጨምሮ በድምሩ የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን አቶ ተፈራ ገልጸዋል።

የችግሩ መንስኤና የደረሱ ጉዳቶች በፖሊስ ተጣርቶ በቀጣይ ዝርዝር መረጃ እንደሚሰጥም ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.