Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል ከግንቦት 1 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓት እንደሚፈፀም ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ከግንቦት 1 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓት እንደሚፈፀም ተገልጿል፡፡
የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኡሌሮ ኡፒዮ(ኢ/ር) እንዳሉት÷ የዲጂታል የክፍያ ሥርዓት እንዲፈጸም የተወሰነው ግብይቱን ዘመናዊ ለማድረግ ብቻ ሳይሆን ከነዳጅ ግብይት ጋር በተያያዘ ያሉ ሕገወጥ ተግባራትን ለመከላከል ነው።
የዲጅታል ስርዓት አሰራሩ አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚሰራም አስረድተዋል።
በቴሌ ኮሙኒኬሽን የደቡብ ምዕራብ ምዕራብ ሪጅን የኢንዳይሬክት ቻናል ሽያጭ ስራ አስኪያጅ ኤርሚያስ አባተ በበኩላቸው ÷ ኢትዮ ቴሌኮም የኔትወርክና ተያያዥ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን እየተከታተለ ተገቢውን አገልገሎት እንዲሰጡ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ማደያ ባለባቸው አካባቢዎች ሁሉ የኔትወርክ ችግር እንዳይኖር ቀደም ተብሎ መሰራቱንም መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትና አደረጃጀት ባለሙያ አቶ ጎይቶም ሃዲስ ÷ የዲጂታል የነዳጅ ግብይትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቃቸውን ነው የተናገሩት።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.