Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመጪው ክረምት የሚተከሉ ከ55 ሚሊየን በላይ ችግኞች እየተዘጋጁ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመጪው ክረምት የሚተከሉ ከ55 ሚሊየን በላይ ችግኞች እየተዘጋጁ መሆኑን የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ እና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ደሳለኝ እንዳሉት÷ ችግኞቹ እየተዘጋጁ ያሉት በ83 የችግኝ ማፊያ ጣቢያዎች ነው።

ችግኞቹ በመጪው ክረምት በአረንጓዴ አሻራ እና በመደበኛ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብሮች የሚተከሉ መሆናቸውንም አመልክተዋል።

በዚህም ቀርቀሃ፣ ማንጎ፣ አቮካዶ፣ ብርቱካን፣ ዘይቱና፣ ቡና እንዲሁም ሌሎች የአገር በቀል ዛፍ ችግኞች እንደሚገኙበት ኢዜአ ዘግቧል።

በክልሉ መደበኛው የችግኝ ተከላ መርሀግብር ከሰኔ 15 እስከ ሐምሌ15 ቀን 2015 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን÷ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብርም ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በክረምት ወራት በመደበኛና በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃግብሮች ከ120 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ችግኞች ተተክለው ከ68 በመቶ በላይ የሚሆኑት እንደፀደቁ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.