Fana: At a Speed of Life!

በሰሜኑ ጦርነት የተጎዱ አከባቢዎችን ተባብረን ማቋቋም አለብን – ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜኑ ጦርነት የተጎዱ አከባቢዎችን ተባብረን ማቋቋም አለብን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

በጦርነት የተጎዱ አከባቢዎችን ለማቋቋም የተዘጋጀ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ከጦርነት አንዳች ትርፍ አይገኝም፤ ከዚያ ይልቅ ብዙ ጎደሎዎችን ያስከትላል ብለዋል፡፡

ያኔ በጥቃቅን ጉዳዮቻችን ጎራ ለይተን ስንነታረክ ጣልቃ ይገቡ የነበሩ ሀገራት አሁን መልሰን እንቋቋም ስንል እነርሱ የሉም ብለዋል ከንቲባዋ በንግግራቸው፡፡

የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ከማጠናከር ጎን ለጎን በግጭቱ የተጎዱ ዜጎች መሰረታዊ አገልግሎት እንዲያገኙ የበኩላችንን ልንወጣ ይገባልም ነው ያሉት።

የድጋፍ ማሰባሰቢያው ይህ የመጀመሪያው መሆኑ እና በቀጣይ በሚከናወኑ መርሐ ግብሮች እንደ አስተዳደር ከ500 ሚሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ መታቀዱ ተገልጿል፡፡

ዛሬ በተካሔደው የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐግብርም በሰሜን ኢትዮጵያ በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች ከ650 ሚሊየን ብር በላይ ለመለገስ ቃል መገባቱን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ድጋፍ ላደረጉ አካላትም ከተማ አስተዳደሩ አመስግኗል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የዕምነት አባቶች፣ ባለሀብቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በወንድሙ አዱኛ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.