Fana: At a Speed of Life!

በወ/ሮ ሙፈሪሃት የተመራ ልዑክ ከትግራይ ክልል የዘርፉ አመራሮች ጋር መከረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የተመራ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ ከትግራይ ክልል ጊዜአዊ አስተዳደር የዘርፉ ቢሮ አመራሮች ጋር በመቀሌ ተወያየ፡፡

በትግራይ ክልል ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ለማሻሻል እንደ ሚኒስቴር ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ የተደረገው ውይይት ውጤታማ መሆኑን የሥራ ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገልጸዋል፡፡

የክህሎት ልማት ሥራችን በክልሉ ያሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን የለየ፣ የዕሴት ሰንሰለትን መሰረት ያደረገ እና ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥር መሆን ይኖርበታል ብለዋል፡፡

በክልሉ መልሶ ግንባታ ሂደት፣ በክህሎት ልማት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የአሠሪና ሠራተኞች ጉዳዮች ምልዑ እንዲሆኑ የሁሉንም ርብርብ ስለሚፈልጉ ባለድርሻና አጋር አካላትን በማቀናጀት ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.