Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ባለፉት 9 ወራት ከ13 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ13 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ይግለጡ አብዛ እንደገለጹት÷ በደቡብ ክልል በዘጠኝ ወራት ከ13 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል፡፡

በበጀት ዓመቱ ከታቀደው 94 በመቶ ገቢ መሰብሰብ እንደተቻለ ጠቅሰው÷ለንግዱ ማህበረሰብ እና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት በገቢ አሰባሰብ ምንነትና ጠቀሜታ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ በመቻሉ በዘርፉ የላቀ አፈጻጸም ተመዝግቧል ብለዋል።

የሚሰበሰበው ገቢ ሀገራዊ እና ክልላዊ የልማት ስራዎችን ለማከናወን እንደሚውልም መገለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በቀጣዮቹ ወራት ዓመታዊ የገቢ አሰባሰብ እቅዱን ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.