Fana: At a Speed of Life!

የመደመር መጽሐፍ የማጠቃለያ አውደ ርዕይ በአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛ ቀኑን የያዘው “ቃል፤ ተግባር፤ ትውልድ” በሚል መሪ ሀሳብ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የመደመር መጽሐፍ የማጠቃለያ አውደ ርዕይ ተጠናቋል፡፡

በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ  መልዕክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ÷ ኢትዮጵያ ላይ እኛ መሠረት ነው የምንጥለው ያሉ ሲሆን  የዛሬ ባለአደራዎች ደግሞ በተሻለ መልኩ ለቀጣይ ትውልድ እንዲያስተላልፉ ጠይቀዋል፡፡

ከማህበራዊ ሚድያ ጋር በተገናኘም ትውልዱ ራሱን ከአጥፊ ነገር በመቆጠብ እየመረጠ ሀገር የሚገነባውን ብቻ ሊወሥድ እንደሚገባው መልክታቸውን አስተላልፈዋል::

በመድረኩ ላይ  በመደመር ትውልድ መጽሐፍ ከተጠቀሱት አምስት ትውልዶች ውስጥ አንዱ በሆነው የመደመር ትውልድ ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ ተካሂዷል።

የመደመር ትውልድ ሁሉም የሚመኛትን ኢትዮጵያ ለመገንባት አቅም ያለውና ለሥኬቱም የሚታትር መሆኑ በውይይቱ የተነሳ ሲሆን÷ አሁን ያለው ትውልድ የመደመር ትውልድን ለመገንባት መሥራት እንደሚገባውም ተመላክቷል፡፡

በመድረኩ ሀሳባቸውን ያጋሩት ታዳጊዎች ለመጽሐፉ ደራሲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  የምስጋና መልዕክታቸውን በደብዳቤ  ማድረሳቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፃፉት እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግሮች የያዙት አነዚሀ መፅሃፎች ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ በአብረሆት ቤተ መፅሃፍ ለሽያጭ ዝግጁ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፃፉት እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግሮች የያዙት እነዚህ መጽሐፎች ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ በአብርሆት ቤተ መፅሃፍት ለሽያጭ እንደሚቀርቡ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.