Fana: At a Speed of Life!

ግብርናን ማዘመን የመንግስት ዋነኛ ትኩረት ነው  -አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብርናን ማዘመን ዋነኛ የመንግስት ትኩረት መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

አቶ ደመቀ ዛሬ በተከፈተው የግብርና እና የሳይንስ አውደርዕይ ላይ እየተካሄደ ባለው የፓናል ውይይት  ግብርና የተፈላጊነቱን ያህል  ውጤት ሊሠጠን የሚችለው በምንሠጠው ልክ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም ግብርናን ማዘመን ዋነኛ ትኩረት ሥለመሆኑ አንስተዋል።

ሀገርን ለመለወጥ ሆነ ሌሎች ነገሮችን ለማሣካት የዘርፉ መዘመን ወሣኝ መሆኑንም በመድረኩ ገልፀዋል፡፡

እንደ አብነትም አሁን ላይ በስንዴ ምርት ላይ የተሠራውን ሥራ አንስተው  ከኛም አለፎ ለሌሎች ምሣሌ መሆን የቻለ ነው ብለዋል።

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ በቴክኖሎጂ ያልታገዘውን የግብርና ሥራ ለማዘመን የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል።

በዚህም ባለፉት ሶስት ዓመታት ለግብርናው ዘርፍ ከ36 ቢሊየን ብር በላይ ድጎማ ተደርጓል ነው ያሉት።

በቀጣይ  የግብርናውን ዘርፍ ከዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ጋር  በማጣመር ለውጥ እንዲያመጣ ይሠራልም ብለዋል።

በታሪኩ ለገሠ እና ሰሎሞን ይታየው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.