Fana: At a Speed of Life!

ፌደራል ፖሊስ በወንጀልን መከላከል ስልጠና የወሰዱ የፖሊስ አባላትን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በአዋሽ ሰባት መሰረታዊ የፖሊስ ስልጠና አካዳሚ ለረጅም ጊዜ ያሰለጠናቸውን በርካታ የወንጀል መከላከል የአድማ ብተና ፖሊስ አባላትን ዛሬ አስመርቋል።

በምረቃ ስነስርዓቱ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የፀጥታና ጥበቃ ዋና መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር  አበራ ሁንዴ÷  ተመራቂዎቹ የፖሊስ አመራርና አባላት ስልጠናውን በሚገባ ተከታትለው በብቃት ያጠናቀቁና የተሰጣቸውን ፈተና በሚገባ  ያለፋ መሆናቸውን ገልፀዋል።

“የሀገራችንን ሰላም እና ፀጥታ በማረጋገጥ ረገድ የፀጥታና ህግ ማስከበር መምሪያ የህግ ማስከበር ስራዎችን በጀግንነት፣ በግልፀኝነትና በቅንነት ስታገለግሉ  ቆይታችሁ ግዳጃችሁን በጥሩ ሥነ-ምግባር ፈፅማችሁ ወደ መጀመሪያው የአድማ ብተና የፖሊስ ሙያ በመመለስ ለቀጣይ ሀገራዊ ተልዕኮ  የተዘጋጃችሁ በመሆናችሁ ኩራት ይገባችኋል “ብለዋል።

በቀጣይ የሚጠብቁን ግዳጆችን በብቃት ለመወጣት ቁርጠኝነት የሚጠይቅ በመሆኑ ሙያዊ ሥነ-ምግባር በተላበሰ ፖሊሳዊ ጨዋነት ከማንኛውም የሀይማኖት፣ የዘርና ፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዳ የፖሊስ አገልግሎት ለመስጠት ከአድማ መከላከልና መቆጣጠር ፖሊስ ይጠበቃል ብለዋል።

ተመራቂዎቹበአድማ ጊዜ ትዕዛዝ አጠባበቅ፣ ተመጣጣኝ እርምጃ አወሳሰድ፣ የእምነት ፣ ትምህርት ቤቶችንና ሆስፒታሎች አካባቢ እንዴት አድማ መከላከልና መቆጣጠር እንደሚገባ፣ አሰላለፍና የተተኳሽ መሳሣሪያ አጠቃቀም፣ ፖሊሳዊ ሰነ-ምግባር ትምህርት፣ በህገ-መንግስት ትምህርት፣ የወንጀል መከላከል ትምህርት፣ የአካል ብቃት ስልጠና መውሰዳቸውን ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.