Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ  ሀገራት በተደረጉ የጎዳና ላይ ውድድሮች  ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ ሀገራት በተደረጉ የጎዳና ላይ ውድድሮች  ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

ትናንት በቼክ ሪፐብሊክ በተደረገ ፕራግ ማራቶን በሴቶች አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ ስታሸንፍ በወንዶች አትሌት ሲሳይ ለማ ሁለተኛ ወጥቷል።

በአሜሪካ በተካሄደው ፒትስበርግ ግማሽ ማራቶን በሴቶች አትሌት ብዙዬ ድሪባ በቀዳሚነት አጠናቃለች።

በቻይና ሻጎን ማራቶን ውድድር  ደግሞ በሴቶች አትሌት አልማዝ ጥላሁንና እታፈራሁ ዱባለ አንደኛና ሁለተኛ በመውጣት ሲያሸንፉ በዛው ሻጎን ከተማ በተደረገ የግማሽ ማራቶን በሴቶች አትሌት ኢብሴ አየለ  እና አትሌት ሂሩት ጀንበሩ አንደኛ እና ሁለተኛ በመውጣት አሸንፈዋል፡፡

በወንዶቹ አትሌት ገመቹ ጊሼና አማን ካዲ አንደኛና ሁለተኛ በመውጣት ውድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል።

በአሜሪካ ስፖኬን ከተማ በተደረገ የ12 ኪሎ ሜትር ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል።

በዚሁ ርቀት በወንዶች አትሌት ጀማል ይመር አንደኛ፣ አትሌት ሞገስ ጥዑማይ ሶስተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ በሴቶች ደግሞ አትሌት የሺ ካላዩ አንደኛ በመውጣት ውድድሩን አሸንፋለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.