Fana: At a Speed of Life!

በቴክሳስ የገበያ ማዕከል 8 ሰዎች በተኩስ እሩምታ መገደላቸው ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቴክሳስ የገበያ ማዕከል ቢያንስ 8 ሰዎች በታጣቂ በተከፈተባቸው የተኩስ እሩምታ መገደላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

በተኩሱ ከተገደሉት ሰዎች በተጨማሪም ሰባት የሚደርሱ ሰዎች መቁሰላቸውን ነው ፖሊስ ያስታወቀው።

በተደረገ የተኩስ ለውውጥም ጥቃት አድራሹ ግለሰብ ወዲያው መገደሉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ባለሥልጣናት ብቻውን እየሠራ ይመስለናል ያሉት እና ዓላማው እስካሁን ያልታወቀው ታጣቂ በአለን ቴክሳስ ከሚገኘው አለን ፕሪሚየም አውትልስ የገበያ ማዕከል ውጭ መተኮስ ከጀመረ በኋላ በፖሊስ መገደሉን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ብሪያን ሃርቪ ተናግረዋል።

የአለን የእሳት አደጋ መከላከያ ክፍል ሃላፊ ጆን ቦይድ በበኩላቸው ተቋማቸው በጥይት የቆሰሉ ቢያንስ ዘጠኝ ተጎጂዎችን ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ገልጸዋል።

ከተጎጂዎች መካከል ሁለቱ በሆስፒታል ውስጥ ህይወታቸው እንዳለፈ መናገራቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።

ከተጎጂዎቹ መካከል ሦስቱ በአስጊ ሁኔታ ላይ ሲሆኑ አራቱ ደግሞ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ነው የተናገሩት።

በአካባቢው 16 ሆስፒታሎችን የሚያስተዳድረው ሜዲካል ሲቲ ሄልዝ ኬር የድንገተኛ ክፍሎቹ ከ5 እስከ 61 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ የቆሰሉ ስምንት ተጎጂዎችን በማከም ላይ መሆናቸውን ገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.