Fana: At a Speed of Life!

በሕገ-ወጥ የወርቅ አምራቾች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል- አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በህገ-ወጥ የወርቅ አምራቾች እና አዘዋዋሪዎችላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።
 
በክልሉ ህገ-ወጥ የወርቅ አምራችና አዘዋዋሪዎችን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ክልላዊ ኮማንድ ፖስት በሸርቆሌ ወረዳ እና አሶሳ ከተማ ከሚገኙ የወርቅ አምራችና አዘዋዋሪዎች ጋር ተወያይቷል።
 
በውይይቱም ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፣ በመከላከያ ሠራዊት የ404 ኮር ዋና አዛዥ ብ/ጄነራል ሰይፈ ኢንጊን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ወርቅ አምራቾችና አዘዋዋሪዎች ተገኝተዋል።
 
አቶ አሻድሊ ሀሰን÷ መንግስት ሕጋዊ የሆኑ የወርቅ አምራቾችንና አዘዋዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የማበረታቻ እርምጃዎች መተግበር ጀምሯል ብለዋል።
 
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ወርቅ አምራቾችና አዘዋዋሪዎች የሚያመርቱትን ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ በማስገባት የማበረታቻው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
 
መንግስት ወርቅ የሚመረትበትን መንገድ ለማዘመን ለወርቅ አምራቾችና አዘዋዋሪዎች እያደረገ ያለው ድጋፍ ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባውን የወርቅ ምርት ለማሣደግ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
 
ከዚህ ውጪ የሚደረግን የወርቅ ግብይት የሀገርን ኢኮኖሚ የሚጎዳ በመሆኑ ኮማንድ ፖስቱ አይታገስም ነው ያሉት፡፡
 
በሕገ-ወጥ የወርቅ አምራቾች እና አዘዋዋሪዎች ላይ እየተወሠደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.