Fana: At a Speed of Life!

ከጅቡቲ ወደ አፋር ክልል የገቡ 336 ዜጎች በአስገዳጅ የለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ አቅጣጫዎች ከጅቡቲ ወደ አፋር ክልል የገቡ 336 ዜጎች በአስገዳጅ የለይቶ ማቆያ እንዲገቡ መደረጉን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለፀ።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ያሲን ሀቢብ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት ከጅቡቲ ወደ ክልሉ በተለያዩ አቅጣጫዎች የሚገቡ ዜጎችን ከክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ እንዲሁም ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ክትትል እየተደረገ ነው።

በዚህም እስካሁን ከጅቡቲ ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ 336 ሰዎች ወደ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደርጓል ብለዋል።

ከዚህ ውስጥ 226 በሰመራ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው የለይቶ ማቆያ እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን፥ 110 ደግሞ በድንበር አካባቢ በተዘጋጁ የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ገብተው በህክምና ባለሙያዎች ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛልም ነው ያሉት።

እስካሁን የ30 ሰዎችን ናሙና በመውሰድ የምርመራ ውጤታቸው እየተጠበቀ ሲሆን በቀጣይም ከ60 ሰዎች ናሙና ለመውሰድ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

በአሊ ሹምባህሪ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.