Fana: At a Speed of Life!

በሕይወትዎ ለውጥ አሥፈላጊ መሆኑን አመላካች ምክንያቶች

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕይወት ውስት ለውጥ የማይቀር ሂደት እና አሥፈላጊ መሆኑ ይታመናል።

ለውጥ ሲባል የነበረውን ጥሎ አዲስ ነገር ከመጀመር ጀምሮ ነገሮችን እያሻሻሉ የሕይወት አካል ማድረግን ያካትታል።

የሥነ-ልቦና ባለሙያዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ለለውጥ አነሳሽ ምክንያቶች መሆናቸውን ይዘረዝራሉ።

አሰልቺ የሕይወት ጉዞ እየተከተሉ እንደሆነ ከተሰማዎ ፦ በተመሳሳይ የሕይወት አዙሪት ውስጥ እንደተቸከሉ የሚሰማዎት ከሆነ ጥቃቅን የሚመስሉ ግን ፍሬያማ ለውጦች ደስታዎን፣ የሥራ ፍላጎትዎን እና ፈጠራዎን ሊመልሷቸው ይችላሉ።

ለዚህ ደግሞ መንቀሳቀስና አዳዲስ ነገሮችን መልመድ አስፈላጊ መሆኑን የሥነ ልቦና ተመራማሪና ባለሙያ ዶክተር አልቼ ቦይስ ይገልጻሉ።

የተለመዱ የዘወትር ሥራዎን በተለየ መልኩ መከወን የዕድገት ዕድልዎን በር ይከፍታልና በሥራዎ ላይ ፈጠራ ያክሉበት።

ፍላጎት ማጣት ወይም መሰላቸት ሲሰማዎ ፦ ያስተውሉ የሚሠሩትን ሥራ ለመጨረስ ብቻ በግዴለሽነት የሚተገብሩት ከሆነ ፣ ሕይወትዎን ፍሬያማ በሚያደርግዎ መሥመር እየመሩ እንዳልሆነ ይገንዘቡ፤ ለውጥ ያስፈልግዎታልና ለለውጥ ይዘጋጁ።

የሥራ ዕድገት ወይም ለውጥ ከሌለ፦ ሰዎች በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው የሥራ ዕድገት ወይም ለውጥ ሲኖር ጥሩ ስሜት ይሰማቸዋል።

ምናልባት ላለፉት ሥድስት ወራት በሕይወትዎ ምንም ዓይነት የሥራ ዕድገት ወይም ለውጥ ከሌለ አልያም ሕይወትን በተለየ መልኩ እንዲረዱ ያስቻለዎ አዲስ ጓደኛ ካላፈሩ ለለውጥ ይዘጋጁ፤

በጭቅጭቅ የተሞላ ምኅዳር ÷ የሚሠሩበት፣ የሚመገቡበት፣ ገንዘብዎን ወይም ጊዜዎን የሚያሳልፉበት ወይም ቤተሰብዎን የሚያስተዳድሩበት ሁኔታ በጭቅጭቅ እና በእርካታ ዕጦት የተሞላ እንደሆነ ይሰማዎታል? ÷ መልስዎ “አዎ” ከሆነ … መቸከልዎን የሚያሳይ ምልክት ነውና ለለውጥ ይዘጋጁ።

ከቤተሰብዎ ጋር ያለዎ ግንኙነት ሲሸረሸር፦ በፍቅር እና በቤተሰብ ኃላፊነት ሕይወትዎ ከአጋርዎ እና ከቤተሰብ አባላት ጋር ያለዎት ትሥሥር እየተሸረሸረ ሲሄድ መነጫነጭ ይጀምራሉ።

እርስዎ መነጫነጭ ጀምረዋል ? መልስዎ አዎ ከሆነ ከመርፈዱ በፊት በፍጥነት ግንኙነትዎን ለማሻሻል ፈጠራ የታከለበት የለውጥ እርምጃዎች ይውሰዱ ፤ (አዝናኝ፣ አዲስ እና ፈታኝ እንቅስቃሴዎችን በጋራ መሥራት ለለውጥ በአብነት ሊጠቀሱ ይችላሉ)

ይተገብሯቸው ከነበሩ መልካም ልማዶችዎ ከራቁ፦ ከረጅም ጊዜ በፊት የነበረዎትን ፍላጎት ወይም ልማድ አቋርጠዋል ? ለምሳሌ መፅሐፍ ማንበብ ፣ ሥዕል መሳል፣ ጂም ወይም ስፖርት መሥራት ሊሆን ይችላል፤ መልስዎ አዎ ከሆነ ምክንያት ሳይደረድሩ ለመጀመር ይዘጋጁ ።

ዕለት ተዕለት ዕሴትዎ እየተሸረሸረ እንዳለ ከተሰማዎ፦ ለምሳሌ ሰውን መርዳት ወይም የሰዎችን ችግር መፍታት የሚያረካዎ ከሆነ እና ምናልባት ከዚህ ልማድዎ ከራቁ ነገሮች እየተበላሹ እንደሆነ ያስቡ።

መሰል ነገሮች ምናልባት ከድግግሞሽና የመሰላቸት አይነት መንፈስ ጋር ተዳምረው ሊከሰቱ ይችላሉ፥ ይህ መሆኑ ቢያንስ አለኝ ከሚሉት መልካም ነገር መስመር እየወጡ ነውና ወደ ነበሩበት የህይወት ጎዳና ይመለሱ።

ምናልባት እነዚህ ነገሮች በህይወትዎ ከተደጋገሙ በጣም ቀላል ከሚሉት የዘወትር የህይወት ዑደት አንድ ብለው ቀስ በቀስ በትንሽ ለውጥ ይጀምሩና በሂደት ከፍ ወዳለው ለውጥ ይሸጋገሩ።

እንደ ሳይኮሎጂ ቱ ደይ መረጃ ለውጥ ሲጀምሩ በተቻለ መጠን ፈጠራንም ቢያክሉበት የተሻለ ይሆናል

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.