Fana: At a Speed of Life!

ብሪታኒያ በትምህርቱ ዘርፍ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ እንደምታጠናክር ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከብሪታኒያ የልማትና የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አንድሪው ሚቼል ጋር መከሩ፡፡

የብሪታኒያው የልማትና የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አንድሪው ሚቼል ከሌሎች የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ጋርም በዘርፉ ያለውን ተግዳሮት አንስተው መወያየታቸውን በብሪታኒያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተለይም ብሪታኒያ የሴቶች ትምህርት ሊሻሻል በሚችልበት ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።

በሚቀጥለው ወርም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በኢትዮጵያ በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ተነግሯል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.