Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የፓናል ውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ”ኢትዮጵያዊ የፖሊሲ ማዕቀፍ ለኢንዱስትሪ ትስስር በሚል መሪ ሃሳብ” የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የፓናል ውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ የግብዓት ትስስር ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል።

እየተካሄደ ባለው የፓናል ውይይት ላይ የአምራች ዘርፉን በግብአት ትስስር በኩል የተሰሩ ስራዎች እና በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች ተገምግመዋል።በውይይቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል፣ የግብርና ሚኒስትር ዲኤታ መለሰ መኮንን (ዶ/ር) እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

በለይኩን አለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.