Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፓኪስታን ካራቺ ከተማ የመጀመሪያውን በረራ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፓኪስታን ካራቺ ከተማ ከ20 ዓመት በኋላ የመጀመሪያውን በረራ  በዛሬው እለት አድርጓል፡፡

አየር መንገዱ ወደ ካራቺ ባደረገው በረራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ፣ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ወደ ፓኪስታን የተጓዙ ሲሆን  ካራቺ ከተማ ሲደርሱም  ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ካራቺ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ በእስያ 37ኛ መዳረሻው ስትሆን አጠቃላይ የሀገር ውስጥ እና ዓለምአቀፍ መዳረሻውን ወደ 145 እንዲያሳድግ አስችሎታል።

በመጀመሪያ በረራ ወደ ካራቺ ያመራው የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችን ልዑካን ቡድን አባላት ዛሬ በሚጀመረው የፓኪስታንና እና ኢትዮጵያ ንግድ ፎረም ላይ እንደሚሳተፍ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.