Fana: At a Speed of Life!

ቢሮው የ6ኛ እና 8 ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ቀናትን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ 6ኛ እና 8 ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ቀናትን ይፋ አድርጓል፡፡

የቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ እንደገለጹት÷ የ 8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 19 እና 20 እንዲሁም የ 6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 26 እና 27 ቀን 2015ዓ.ም ይሰጣል::

ቢሮው ከተማ አቀፍ ፈተናዎቹን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱንም ነው አቶ ዲናኦል የተናገሩት ፡፡

በ2015ዓ.ም 75 ሺህ 100 የ8ኛ ክፍል እንዲሁም 75 ሺህ 78 የ 6ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተናውን እንደሚወስዱ ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹን የበለጠ ማዘጋጀት እንዲችሉ ከከተማና ክፍለ ከተሞች ጋር በጋራ በመሆን የሞዴል ፈተናዎችን እንዲሰጡም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል ::

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.