Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ፖሊስ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የ8 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተለያዩ አካባቢዎች በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ሥምንት ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ፣ በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን እና በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤልድ ጋፉን ለተወካዮቹ ባስረከቡበት ወቅት እንዳሉት÷ ሠራዊቱ ችግሩን እንደ ራሱ ችግር ቆጥሮ በፍላጎቱ ከደመወዙ አዋጥቶ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል፡፡

በቀጣይም በድርቅ የተጎዱ ዜጎችን ከዚህ ችግር ወጥተው ወደ ዘላቂ ልማት እስኪገቡ ድረስ የበኩላቸውን እገዛ ለማድረግ ዝግጁ ነን ማለታቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.