Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር  ሽብሩ ማሞ  ከዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የሥራ ኃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር  ሽብሩ ማሞ  ከዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የታንዛንያ ተወካይ ማውሪዚዮ ቡሳቲ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በታንዛኒያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን

ፍለስተኞች

ወደ አገራቸው  መመለስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ  ምክክር አደርገዋል፡፡

አምባሳደር ሽብሩ ÷ የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ  ዜጎችን  ወደ አገር ቤት ለመመለስ ቀደም ብሎ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተዋል።

ለዚህም የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን የገለፁት አምባሳደሩ÷ ዜጎች በእስር ቤት ቆያታቸው ሰብአዊ መብታቸው መጠበቅ እንዳለበት  አስገንዝበዋል።

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በእስር ላይ ረዥም ጊዜ የቆዩና ለታማሚዎች ቅድሚያ መሰጠት እንዳለበትም አሳስበዋል።

በዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የታንዛኒያ ተወካይ  ማውሪዚዮ ቡሳቲ  በበኩላቸው ÷ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የብዙ ሀገር ዜጎች በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ታንዛኒያ ገብተው በሀገሪቱ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አንስተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት አስቸኳይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የዓለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት ጥረት እንደሚያደርግ መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.