Fana: At a Speed of Life!

የደቡብና ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የቲቢ ፕሮግራም የጥናት ጥምረት የመጀመሪያ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብና ምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የቲቢ ፕሮግራም የጥናት ጥምረት የመጀመሪያ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት፣ ከጤና ሚኒስቴርና ከዓለም ጤና ድርጅት ትሮፒካል ዲዚዝ ሪሰርች ጋራ በመሆን ያዘጋጁት መድረክ ነው፡፡

ከደቡብ እና ምስራቅ አፍሪካ የተውጣጡ 22 ሀገራት በቲቢ ላይ ያላቸውን ልምድ ልውውጥ ለማድረግ እንዲሁም በሽታውን ለመግታት እየሰሯቸው ስላሉ ስራዎች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና መፍትሄዎች ላይ ለመወያየት የሚያስችል መድረክ መሆኑም ተገልጿል።

የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ፥ የቲቢ በሽታ የዘመናችን ገዳይ በሽታ መሆኑንና በዓለም 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሠዎች በቲቪ እንደሚሞቱ ጠቁመዋል፡፡

10 ሚሊየን ሠዎች በየዓመቱ በበሽታው እንደሚያዙ ጠቅሰው፥ የቲቢ መከላከል ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ የመከላከል፣ የመመርመርና የማከም ስራዎች እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ተወካይ ዶክተር አበራ በቀለ ፥ ኢትዮጵያ ላለፉት 20 ዓመታት ህክምናውን በማስፋፋትና ጥራቱን በማስጠበቅ፣ የቲቪ ታማሚዎችና የሞት ቀጥር በመቀነስ ረገድ በርካታ ስራዎች መስራት ብትችልም ከጎረቤት ሀገራት ባለው ድንበር ተሻጋሪ የሰዎች ዝወውር ምክንያት መድሀኒት የተላመደ ቲቢ መቆጣጠር አደጋች ሆኖ መቆየቱን ተናግረዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶክተር ኖን ሀልንሀላ ዲላሚኒ ፥ የደቡብና ምስራቅ አፍሪካ አዲሱ የቲቪ ጥምረት ውጤታማ ሥራዎችን እንደሚሠራ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

አክለውም በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚሰራው ስራ ላይ የዓለም ጤና ድርጅት እገዛ ለማድረግ ቁርጠኛ ነው ማለታቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

በጤና ሚኒስቴር የቲቢ፣ ስጋ ደዌና ሌሎች የሳንባ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዴስክ ኃላፊ አቶ ታዬ ለታ ፥ ኢትዮጵያ ቲቢ ጫና ካሳረፈባቸው 30 ሀገራት አንዷ መሆኗን ጠቅሠው ይህን ለማስተካከል በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ እንዳለም ገልጸዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.