Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ በነዳጅ ግብይት ከአውሮፓ ኅብረት ጋር እየተለያየች ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራባውያንን ማዕቀብ ተከትሎ ሩሲያ ወደ ላቲን አሜሪካ የምትልከውን የነዳጅ አቅርቦት መጠን ማሳደጓ ተገለጸ፡፡

አሁን ላይ የወጣው የቁጥር መረጃ እንደሚያመለክተው በፈረንጆቹ ሚያዝያ ወር ላይ ሩሲያ ፕሪሞርስክ ከተሰኘው የባልቲክ ወደቧ ሁለት 73 ሺህ ያኅል ቶን ነዳጅ የጫኑ መርከቦቿ ወደ ቺሊ ጉዋያካን ወደብ አቅንተዋል፡፡

ሩሲያ ከፈረንጆቹ ጥር ወር እስከ ሚያዝያ ድረስ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ቶን ያኅል ነዳጅ ወደ ላቲን አሜሪካ ሀገራት በተለይም ወደ ብራዚል መላኳ ነው የተገለጸው።

አኀዙ እንደሚያመላክተው ሩሲያ በፈረንጆቹ 2011 ላይ ወደ ቀጣናው ከላከችው 211 ሺህ ቶን የነዳጅ አቅርቦት አንጻር እጅግ ከፍተኛው ነው፡፡

ለበርካታ አሥርት ዓመታት ሩሲያ የአውሮፓ ዋና የነዳጅ አቅራቢ እንደነበረች አስታውሶ የዘገበው አር ቲ ነው፡፡

የዜና ምንጩ የሁለቱ ጎራዎች የቆየ እና የተሰናሰለ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት በወቅታዊ ፖለቲካዊ ተፅዕኖዎች ሥር መውደቁ የአውሮፓ ሀገራት እንደፈለጉ ሲቀዱ የነበረውን ነዳጅ በቁጠባ ለመጠቀም ሲታገሉ እንዲታዩ እያደረገ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

በፈረንጆቹ የካቲት 5 መተግበር የጀመረው የአውሮፓ ኅብረት የነዳጅ ማዕቀብ እንደታሰበው ሩሲያ ላይ ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ ከማሳደር ይልቅ የኅብረቱን አባል ሀገራት ለጉዳት የዳረገ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ይልቁንም ሩሲያ የነዳጅ አቅርቦቷን ወደ እስያ ሀገራት ብቻ ሳይሆን ወደ አፍሪካና መካከለኛው ምሥራቅ ብሎም ወደ ላቲን አሜሪካ በማዞር አዲስ የገበያ ዕድሎችን እንድታይ አድርጓታል ነው የተባለው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.