Fana: At a Speed of Life!

ለገበታ ለትውልድ ፕሮጄክት የሚደረገው ድጋፍ ቀጥሏል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ተቋማት ለገበታ ለትውልድ የሚያደርጉት የገንዘብ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በ14ኛው ዙር የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትና ድርጅቶችን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ኦቪድ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር 30 ሚሊየን ብር፣ የኢትዮጵያ አግሪካልቸራል ቢዝነስ 20 ሚሊየን 500 ሺህ ብር እንዲሁም የትምህርት ቁሳቁስ ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት 10 ሚሊየን 400 ሺህ ብር ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም ዓለማየሁ ከተማ 10 ሚሊየን ብር፣ ኤም ኤስ ኤ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር 10 ሚሊየን ብር፣ አሰር ኮንስትራክሽን 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረጉ ተቋማት ናቸው፡፡

በተመሳሳይ ለፕሮጀክቱ መሳካት አስተዋጽዖ አደርጋለሁ በማለት አንቴክስ ቴክስታይል 6 ሚሊየን ብር ፣ ኮርቴቫ ፓዮናር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር 5 ሚሊየን ብር፣ ሐንሳ ግሩፕ 5 ሚሊየን ብር፣ ኤኪው ሮዝ ኃየተ የግል ማህበር 5 ሚሊየን ብር፣ ሐምበርግ ሮዝስ 5 ሚሊየን ብር፣ አርቫይንድላይፍስታይል አፓረል ማኑፋክቸሪንግ ኃየተ የገል ማኅበር 5 ሚሊየን ብር፣ ከንቲቻ ማይኒንግ 5 ሚሊየን ብር፣ ቻይና ሬይል ዌይ 21ስት ኢንጂነሪንግ ግሩፕ 5 ሚሊየን ብር እንዲሁም ሁዋዌ 5 ሚሊየን ብር ቃል ገብተዋል፡፡

እስካሁን ለገበታ ትውልድ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በአጠቃላይ 7 ቢሊየን 401 ሚሊየን 625 ሺህ 232 ብር ተሰብስቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.