Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ2ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ከነዋሪውና ከንግዱ ማህበረሰብ ገቢን በመሰብሰብ ለከተማው ኢኮኖሚያዊ እድገት መሳካት ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሃመድ ተናግረዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2015 በጀት ዓመት ያለፉትን ዘጠኝ ወራት ከቀጥተኛ፣ ቀጥተኛ ካልሆኑና ታክስ ካልሆኑ እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤታዊ ታክስና ገቢ 2 ቢሊየን 145 ሚሊየን 618 ሺህ 574 ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በዚህም 2 ቢሊየን 564 ሚሊየን 188 ሺህ 252 ብር ገቢ መሰብሰብ እንደተቻለም ነው ዋና ዳይሬክተር የገለጹት ።

የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀርም የ1 ቢሊየን 21 ሚሊየን 181 ሺህ 307 ብር ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

ይህም ውጤት እንዲመዘገብ የድሬዳዋ አስተዳደር ፣ ግብር ከፋዩ ማህበረሰብና የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባለሙያዎችና አመራሮች ከፍተኛ አስተዋፆ ማበርከታቸውን ተናግረዋል ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በተያዘው በጀት ዓመት ከሦስት ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ አቅጄ እየተንቀሳቀስኩ ነውም ብሏል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.