Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ የቴክኖሎጂ ትራንስፎርሜሽንን ለማምጣት እየሰራች ነው – በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ የቴክኖሎጂ ትራንስፎርሜሽንን ለማምጣት እየሰራች መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የአፍሪካ የግብርና ቴክኖሎጂ ፋውንዴሽን የአምስት ዓመት ስትራቴጂ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ÷የአፍሪካ ቴክኖሎጂ ፋውንዴሽን የአምስት ዓመት (2023-2027) ስትራቴጂውን በኢትዮጵያ ማስጀመሩ ልዩ ትርጉም አለው ብለዋል።

ስትራቴጂው የአፍሪካን እድገትና ልማት በቴክኖሎጂ ለማረጋገጥ ከፍተኛ ቁርጠኝነት ያለው በመሆኑ ለተፈጻሚነቱና በዜጎች ላይ ትራንስፎርሜሽን ለማምጣት መነሳሳት ፈጥሮልናል ነው ያሉት፡፡

ሚኒስቴሩ  ከኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት እና ከአፍሪካ ቴክኖሎጂ ፋውንዴሽን ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በቴክኖሎጂ መስክ የተወጠኑ አንዳንድ ሃሳቦችን ለመተግበር፣ አፍሪካ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንደምትችል ማሳየት አለብን ማለታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.