ጠ/ሚ ዐቢይ ከአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ አባላት፣ ከሀገራት መሪዎችና ከ20 በላይ አፍሪካውያን የንግድ ሰዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ አባላት፣ ከሀገራት መሪዎችና ከ20 በላይ አፍሪካውያን የንግድ ሰዎች ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸውም የግሉ ዘርፍ የኮቪድ19ን ቀውስ ከመቋቋም አንጻር ያለውን ሚናን በተመለከተ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።
በጉዳዩ ላይም “ከአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ አባላት፣ ከሀገራት መሪዎች እና ከ20 ከሚበልጡ አፍሪካውያን የንግድ ሰዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል” ብለዋል።
የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ የአፍሪካ የወጪ እና የገቢ ንግድ ባንክ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለአፍሪካ ኮቪድ ፈንድ፣ ለአፍሪካ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል ድጋፍ ለማድረግ ያላቸው ቁርጠኝነት የሚደነቅ መሆኑንም አንስተዋል።
“እንደ አህጉር የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከሉን ማጠናክር እንዲሁም ቫይረሱን የመመርመር አቅማችንን ማጎልበት በእጅጉ ያስፈልገናል” ሲሉም አስታውቅዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision