Fana: At a Speed of Life!

52ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከግንቦት 8 ጀምሮ ይካሄዳል

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 52ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከግንቦት 8 ጀምሮ በኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ ይካሄዳል።

ውድድሩን አስመልክቶ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዓላማ አትሌቶች የስልጠና ልምምዳቸውን አቋም የሚለኩበትና ተተኪ አትሌቶች ለማፍራት የሚረዳ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በሀንጋሪ ቡዳፔስት በሚካሄደዉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች እንደሚመረጡ የኢትዮትዮጵያ አትሌቲከስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

በሻምፒዮናው ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ሽልማት ለአትሌቶቹ መዘጋጀቱንና ፌዴሬሽኑ በአጠቃላይ ለውድድሩ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ በጀት መመደቡን አመልክቷል።

ከ11 ክልሎች፣ ሁለት ከተማ አስተዳደር፣ 30 ክለቦችና ተቋማት የተውጣጡ በአጠቃላይ በሁለቱም ፆታ 1 ሺህ 270 አትሌቶች በሻምፒዮናው ላይ እንደሚሳተፉ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

በውድድሩ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ የሚወጡ አትሌቶችም ለ19ኛው የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ለመወከል ሐዋሳ ላይ በሚካሄደው የሰዓት ማሟያ ዉድድር ላይ ለመሳተፍ እንደሚመረጡ ተገልጿል።

52ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከግንቦት 8 እስከ ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ይቆያል።

51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሐዋሳ ከተማ የተካሄደ ሲሆን÷መቻል ስፖርት ክለብ የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ1963 ዓ.ም መጀመሩን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.