Fana: At a Speed of Life!

ክሮሽያ በኢትዮጵያ ኤምባሲዋን ልትከፍት ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ዘነበ ከበደ ከክሮሽያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋና ዳይሬክተር ፔታር ሚሃቶቭ ጋር ተወያይተዋል፡፡
.
በውይይታቸውም÷ በሁለትዮሽ ግንኙነትን፣ በኢኮኖሚ እና ሌሎች የጋራ ዘርፎች ላይ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
 
አምባሰደር ዘነበ ክሮሽያ በአዲስ አበባ ኤምባሲዋን ለመክፈት መወሰኗ እንዳስደሰታቸው መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አምባሳደሩ በቀጠናው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ኢትዮጵያ ቁልፍ ሚና የምትጫዎት ሀገር መሆኗን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
 
ኢትዮጵያ እና ክሮሽያ በቡና፣ ቆዳ እና ጨርቃ ጨርቅ ዘርፎች ያላቸውን የንግድ ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይም መክረዋል፡፡
በቀጣይም የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እና ሚኒስትሮችን ያሳተፈ ውይይት ለማድረግ መስማማታቸው ነው የተገለጸው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.