Fana: At a Speed of Life!

በሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል 30 ኪሎ ግራም የሚመዝን እንቁልጢ በቀዶ ጥገና ሕክምና ተወገደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል 30 ኪሎ ግራም የሚመዝን እንቁልጢ (Ovarian Tumer) በቀዶ ጥገና ሕክምና መወገዱ ተገለጸ፡፡

የሆስፒታሉ የማሕጸንና ጽንስ እስፔሻሊስት ዶክተር ግላንዴ ግሎ፥ የቀዶ ጥገና ሕክምናው 1 ሠዓት ከ30 ደቂቃ የፈጀ መሆኑን ገልጸዋል።

አሁን ላይ ታካሚዋም በሙሉ ጤንነት ላይ እንደምትገኝ ተነግሯል፡፡

ዶክተር ግላንዴ የማሕፀን ዕጢ ብዙ ጊዜ በመውለድ ዕድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ሴቶች የተለመደ ቢሆንም አልፎ አልፎ ግን ህፃናት እንዲሁም የወር አበባ ማየት ያቆሙ ሴቶች ጭምር ላይ ሊከሰት እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን እስከ አሁን ከ15 ኪሎግራም በላይ የሚመዝን ዕጢ እምብዛም ያልተለመደ ነው ማለታቸውን ከጎፋ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.