Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከከተማዋ ከተውጣጡ ሴቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከከተማዋ ከተውጣጡ ሴቶች ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ “ብልፅግና ለሴቶች፤ ሴቶች ለብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው።

ተወያዮቹ በከተማዋ ሴቶችን ለማብቃት እየተሰራ ያለውን ስራ አበረታተዋል።

አቅም ያልፈጠሩ የሼድ ተጠቃሚዎች ምን ታስቧል፣ ዘመኑ የቴክኖሎጂ በመሆኑ እናቶችን በቴክኖሎጂ እንዲገበያዩ ስልጠና ቢሰጠን፣ የህፃናት ማቆያ በተለያዩ አካባቢዎች ቢገነባ፣ ሴቶች የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።

በውይይቱ ላይ ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ከ15 ሺህ በላይ ሴቶች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ÷ በሰው ተኮር የልማት ስራዎች በተጨባጭ የሴቶችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ሰፊ ሥራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል፡፡

በተማሪዎች እና በተስፉ ብርሃን የምገባ ስራዎች፣ በዳቦ ፋብሪካዎች፣ በእንጀራ ፋብሪካ፣ በሸክላና በሸማ ስራዎች እንዲሁም ከተማ አስተዳደሩ ባስገነባቸው 20ሺህ የአቅመ ደካማ የመኖሪያ ቤቶች የሴቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ቀዳሚ አጀንዳ ተደርጎ መሰራቱን ከንቲባዋ አንስተዋል፡፡

በቀጣይነትም ለማህበረሰቡ ልማትና ብልጽግና አስተዋጽዖ እያበረከቱ ያሉትን ሴቶች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን በስፋት እንሰራለን ሲሉም ገልጸዋል።

በፈቲያ አብደላ እና ማርታ ጌታቸው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.