Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ሕዝብ የዘመን መለወጫ “ፊቼ ጨምበላላ” በዓል በአዲስ አበባ ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ሕዝብ የዘመን መለወጫ የሆነውና በተመድ የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰሱ ቅርሶች የተመዘገበው “ፊቼ ጨምበላላ” በአዲስ አበባ ተከብሯል።

በወዳጅነት አደባባይ በተከበረው “ፊቼ ጨምበላላ” በዓል ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር፣ ሚኒስትሮች፣ የሲዳማ አገር ሽማግሌዎች እና የክልሉ ተወላጆች ተገኝተዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ኢትዮጵያ የብዙ ባህልና ትውፊቶች ባለቤት ናት ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በዩኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት ከተመዘገቡ አኩሪ ቅርሶቻችን መካከል አንዱ እና የሰላም የአንድነት ፣የፍቅር ተምሳሌት የሆነው የፍቼ-ጫምባላላ በዓልን በአዲስ አበባ አክብረናል ብለዋል፡፡

የጋራ ቤታችን በሆነችው አዲስ አበባ ባህሎቻችንን የሚያስተዋውቁና እኛነታችንን የሚያሳዩ እሴቶቻችንን ለማሳደግ እና ከትውልድ ወደትውልድ ለማሸጋገር በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ነው ያሉት፡፡

በዓሉ የሲዳማን ባህላዊ እሴቶችና ማህበራዊ ክዋኔዎች በሚያሳዩ የተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.