Fana: At a Speed of Life!

ጀርመን ለዩክሬን ከፍተኛ የተባለውን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀርመን ÷ ለዩክሬን 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ዩሮ የሚያወጣ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ይፋ አድርጋለች፡፡

ድጋፉ የሆነው የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በተያዘው ሳምንት በበርሊን የስራ ጉብኝት ለማድረግ ማቀዳቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል ፡፡

የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ቦሪስ ፒስቶሪየስ እንዳስታወቁት ÷ ሀገራቸው ለዩክሬን የምታደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች፡፡

አሁን ላይም ጀርመን ለዩክሬን የ2 ነጥብ 7 ቢሊየን ዩሮ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ይፋ ማድረጓን ነው ያረጋገጡት፡፡

ይህም እስካሁን ለዩክሬን ከተሰጡ የጦር መሳሪያ ድጋፎች ከፍተኛ ነው መባሉን ብሉምበርግ በዘገባው አስፍሯል፡፡

የተደረገው ድጋፍ ድሮኖችን እና ታንኮችን ጨምሮ ሌሎች ዘመኑን የዋጁ የጦር መሳሪያዎችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በዛሬው ዕለት በጣሊያን ሮም ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ እንደሚገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.