Fana: At a Speed of Life!

ከአየር ብክለት ነፃ የአውሮፕላን ነዳጅ በሀገር ውስጥ ለማምረት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአየር ብክለት ነፃ የሆነ የአውሮፕላን ነዳጅ በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል እንቅስቃሴ መጀመሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄ÷ አየር መንገዱ ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ተለዋዋጭ ምህዳሮች በመቃኘት ከወቅቱ ጋር የሚራመድና ዘመናዊ አሠራርን እየተከተለ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም÷ የአየር ብክለት ተጽዕኖ የሌለው የአውሮፕላን ነዳጅ በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል ጥናት መጠናቀቁን ጠቅሰዋል፡፡

ከጥናቱ በመነሳት ከሚመለከታቸው የመንግሥትና የግል ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተገብቷልም ነው ያሉት።

ለስኬቱም የቦይንግ፣ የኤር ባስ እና የአያታ የአውሮፕላን ኩባንያዎች እገዛ እያደረጉልን ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት÷ ከአየር ብክለት ነፃ የሆነውን የአውሮፕላን ነዳጅ በሀገር ውስጥ ለማምረት ከነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶችና ከቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በቅርበት እየሰራ ነው፡፡

ከአየር ብክለት ነፃ የሆነ የአውሮፕላን ነዳጅ ከመኖ ተረፈ ምርት የሚዘጋጅ ሲሆን÷በየህይወት ዑደት ተፈጥሮን በማዛባት የሚደርሰውን የካርቦን ልቀት የሚያስቀር ይሆናል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.