Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ ህዝቦች ከልሂቃንና ፖለቲከኞች በተጨማሪ በሀገራቸው ጉዳይ ሀሳብ እንዲሰጡ ለማስቻል እየሰራ ነው – መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ህዝቦች ከልሂቃንና ፖለቲከኞች በተጨማሪ በሀገራቸው ጉዳይ ሀሳብ እንዲሰጡ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ገለፁ።

የምክክር ኮሚሽኑ ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋና ምስራቅ ቦረና ዞኖች ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ ከተማ እየመከረ ነው።

በመድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) እንደገለፁት÷ ኮሚሽኑ ከልሂቃንና ፖለቲከኞች በተጨማሪ ህዝቦች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ሀሳብ እንዲሰጡ ለማስቻል እየሰራ ነው።

የዛሬው መድረክም ባለድርሻ አካላት በተሳታፊዎች ልየታና በአጀንዳ ማሰባሰብ ዙሪያ ግልጽ ግንዛቤ እንዲይዙና በምክክሩ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማስቻል ነው ብለዋል።

መድረኩ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አረጋውያን፣ የሲቪክና ህዝባዊ ተቋማት፣ የፖለቲካ አካላት የሚሳተፉበት እንደሆነ መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም ሁሉም ተሳታፊዎች በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አጀንዳዎች ላይ ግብዓት እንዲሰጡ የተዘጋጀ እንደሆነም ገልጸዋል።

”ሁሉም ስለ ሀገሩ ሀሳብ መስጠት አለበት” ያሉት ሰብሳቢው÷ ሁሉንም የሕብረተስብ ክፍል በማሳተፍ መሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ሀሳብ በማውጣት በምክክር ወደ አንድ ማምጣት መሆኑንም ተናግረዋል።

በዚህም የምክክር ሂደቱ ከአጀንዳ አሰባሰብ ሂደቱ ጀምሮ አካታችና አሳታፊ እንዲሆን ኮሚሽኑ በሙሉ አቅሙ እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.