Fana: At a Speed of Life!

በሶማሊያ የተሰማራው የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ሰራዊት ግዳጁን በብቃት እየፈፀመ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ የተሰማራው የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ሰራዊት ግዳጁን በብቃትና በጀግንነት እየፈፀመ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሀመድ ዋሬ ፣በሶማሊያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ ሜጄር ጄኔራል አማረ ገብሩ እና ከፍተኛ አመራሮች በሶማሊያ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት የግዳጅ አፈፃፀም ጎብኝተዋል ።

የሴክተር ሶስት አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል በስፋት ፈንቴ በሶማሊያ አጠቃላይ የተሰማሩ የሠላም አስከባሪዎች በየሴክተሩ የሰሯቸውን ስራዎች በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል ።

የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት የአልሸባብ ቡድንን በመፋለም እና በተለይም ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ አስተዋፅዖው የጎላ መሆኑንም አምባሳደር ሙክታር መሀመድ ተናግረዋል።

ሰላም አስከባሪ ሃይሉ ለሶማሊያ ህዝብና መንግስት እያደረገ ያለው አስተዋፅኦ የሚደነቅ ነው ያሉት አምባሳደሩ ÷በቀጣይም ከፀጥታ ሃይሉ እና ከባለድርሻ አካላት ጋርበመስራት አህጉራዊ ተልዕኳቸውን በጀግንነት እንዲፈጽሙ አሳስበዋል፡፡

ሜጀር ጄኔራል አማረ ገብሩ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሠላም ማስከበር ተልዕኮ እያደረገች ያለውን ተሳትፎ ይበልጥ አጠናክራ እንድትቀጥል ጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.