Fana: At a Speed of Life!

ለመዲናዋ በጎ ፈቃደኞች እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2014 እና በ2015 ዓ.ም የክረምት ወራት በበጎ ፈቃድ ስራዎች ለተሳተፉ በጎ ፍቃደኞች እውቅና ሰጥቷል፡፡

በመዲናዋ የበጎ ፍቃድ ስራዎች የበርካታ ነዋሪዎች ችግር መቅረፍ መቻሉን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ለሀገር ባለውለታዎችና አቅመ ደካማ ነዋሪዎች ከከተማዋ ዕድገት ፍትሀዊ ተጠቃሚ በማድረግ ማህበራዊ ፍትህ የማንገስ ታላቅ ስራ ተሰርቷልም ነው ያሉት፡፡

በዚህ ታላቅ የበጎነት ተግባር በቀናነት እገዛ ላደረጉ እንዲሁም በበጎ ፈቃደኛነት ለተሳተፉ ወጣቶች ከንቲባዋ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ለከተማዋ ታላቅነት የላቀ አስተዋጽዖ ያላቸውን ታላላቅ ፕሮጀክቶች በጥራትና በጊዜ በመገንባት እና ሰው ተኮር ስራዎችን በመስራት ለኑሮ ምቹ የሆነች ከተማን የመገንባት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከንቲባ አዳነች አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.