Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የግንባታ ሒደትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ቀሪ የግንባታ ስራ ያለበትን ደረጃ ጎብኝተዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማሕበራዊ ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ ስዩም መኮንን፣ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ እርዚቅ ኢሳን ጨምሮ ሌሎች የክልል አፍተኛ  የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ዝቅተኛውን የፊፋ መስፈርት ማሟላት የሚያስችለውን የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ግንባታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ተብሏል።

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃ ከፋለ (ዶ/ር) የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የግንባታ ሒደት አበረታች ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ቀሪ ስራዎችን ባጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ የሰው ኃይልና አስፈላጊ ግብዓት ማሟላት ያስፈልጋል ማለታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የስታዲየሙ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ተፈላጊውን አገልግሎት እንዲሰጥ የሚደረገው ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.