Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ባለሐብቶች በኢትዮጵያ ያላቸውን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሠራ ነው – አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ባለሐብቶች በኢትዮጵያ ያላቸውን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን ገለጹ።

አሁን ላይ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በተለያዩ የትብብር መስኮች ይበልጥ እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ በርካታ የኢንቨስትመንት አማራጮች መኖራቸውን ጠቁመው÷ በተለይም በግብርና እና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ዕድሎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ በዘርፉ ያወጣችው አመቺ ፖሊሲና ስትራቴጂ እንዲሁም ያላት በርካታ የሰው ኃይል ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እንደሚያደርጋትም ጠቁመዋል።

በተፈጠረው ምቹ ዕድልም የቻይና ባለሐብቶች በመጠቀም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በስፋት መሰማራታቸውን እና ተሳትፏቸውም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን አንስተዋል፡፡

የቻይና ባለሐብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያላቸው ተሳትፎ እንዲያድግ ኤምባሲው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር እየሰራ እንደሆነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትሥሥር ለማጠናከር በተሰራው ስራም በርካታ ቻይናውያን ኢትዮጵያን ለመጎብኘትና በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት እያሳዩ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.