Fana: At a Speed of Life!

ጤና ሚኒስቴር በትግራይ ለሚገኙ ጤና ተቋማት የሕክምና መሳሪያ ድጋፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤና ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ለሚገኙ ጤና ተቋማት መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ማስጀመር የሚያስችሉ የሕክምና መሳሪያዎች እና መድሃኒት አስረክቧል፡፡

የሚኒስቴሩ የልዑካን ቡድን አባላት በክልሉ ጤና ተቋማት ላይ የደረሰው ጉዳት አስከፊ መሆኑን በመገንዘብ አፋጣኝ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ያሉ ሆስፒታሎች ከአዲስ አበባና ከፌዴራል ሆስፒታሎች ጋር ጥምረት እንዲፈጥሩ በማድረግ ያሰባሰበውን ድጋፍ በዛሬው ዕለት አስረክቧል ።

ድጋፉን ያስረከቡት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ ÷በክልሉ ያሉ የሕክምና ተቋማት በጦርነቱ የደረሰባቸው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ድጋፉ ከዚህ ቀደም በአማራና አፋር ክልሎች የሚገኙ የጤና ተቋማትን ለማገዝ ሆስፒታሎችን በማጣመር የተሰራው ስራ ያስገኘውን ውጤት መነሻ በማድረግ የተሰበሰበ መሆኑ ተመላክቷል ።

በበርናባስ ተስፋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.