Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በየዓመቱ 77 ሺህ አዳዲስ ዜጎች በካንሰር ሕመም ይያዛሉ – ዶ/ር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የካንሰር በሽታን መከላከል እና መቆጣጠር የሚያስችል የምርምር ጥምረት እና የካንሰር መረጃዎች መዛግብት ጥምረት ጉባኤ ተጀምሯል፡፡

በመድረኩ አምስት የአፍሪካ ሀገራት የተጣመሩበት የካንሰር በሽታን መከላከል እና መቆጣጠር የሚያስችል የምርምር ስራ ይፋ ተደርጓል፡፡

አጠቃላይ ስራውንም ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ አስተባባሪነት በኩል እንደምትመራው የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንደተናገሩት÷ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት በዓመት 533 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች በካንሰር በሽታ ሳቢያ ለህልፈት ይዳረጋሉ፡፡

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ወደ 77 ሺህ የሚጠጉ አዳዲስ የካንሰር ህመምተኞች መኖራቸውን አንስተው÷ በተለይ በሽታው ሴቶችን የጡት እና የማህፀን በር ካንሰር ሰለባ በማድረግ ለስቃይ እንደሚዳርግ ተናግረዋል፡፡

ጥምረቱ በዋናነት በሴቶች ላይ የሚከሰተውን እና በርካቶችን ለህመም እና ለሞት የሚዳርገውን የጡት እና የማህፀን በር ካንሰር በሽታ ለመከላከል ከፍተኛ ድርሻ በመያዝ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የካንሰር ክትትል ውጤታማነት በጥምረቱ አማካኝነት ተግዳሮቶችን ለመለየትና ለመቅረፍ ድጋፍ እንደሚያደረግም ገልፀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.