Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ አፍሪካ የፓርላማ ልዑክ ለልምድ ልውውጥ ኢትዮጵያ ገባ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካ የፓርላማ ልዑክ ከኢትዮጵያ ፓርላማ ጋር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ አዲስ አበባ ገብቷል።

በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ምህረቱ ሻንቆ (ረ/ፕ) ለልዑካን ቡድኑ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ለልዑካን በድኑ አቀባበል ባደረጉበት ወቅት ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ገልፀዋል።

የሁለቱ ሀገራት ምክር ቤቶች ያላቸውን ልምድ የሚለዋወጡበት መልካም አጋጣሚ እንደሆነ የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው፥ በሀገራቱ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ የበለጠ በትብብር ለመስራት ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ በፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥተው በትበብር እንደሚሰሩ የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው ልምድ ሠልውውጡ ጠቃሚ ግብዓቶች የሚገኙበት እንደሆነ አንስተዋል።

በደቡብ አፍሪካ ፓርላማ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ጀምስ ንክሳማሎ ለልዑካን ቡድኑ ስለተደረገው አቀባበል በማመስገን፥ የሁለቱ ሀገራት ምክር ቤት አባላት የሚያደርጉት የልምድ ልውውጥ ዋና አላማው የወከላቸውን ሕዝብ በብቃት እንዲያገለግሉ ለማስቻል ነው ብለዋል።

ሀገራቱ በጋራ የሚያከናውኗቸው በርካታ ተግባራት መኖራቸውን የገለጹት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትሩ÷ በምክርቤታዊ አሰራሮች ዙሪያ በሚካሄዱ የልምድ ልውውጥ ውይይት ጠቃሚ ግብዓቶች የሚገኙበት እንደሆነ መናገራቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.